ከኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይረክቶሬት ለተገልጋዮች የሚሰጥ አገልግሎት እና ተገልጋዮች እንዲያሟሉ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፡-

ሀ. በዳይረክቶሬት የሚሰጡ ዋና ዋና  አገልግሎቶች፡-

  • የኢንቨስትመንት ፈቃድ አዉጥተዉ በዉላቸዉ መሠረት ሥራ ለጀመሩ  ባለሀብቶች  ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚዉል  ተሽከርካሪ  ወይም ካፒታል ዕቃ እንድሁም አክሰሰሪ በደንብና መመርያ በሚፈቅደዉ አግባብ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲያገኙ ድጋፍ መስጠት
  • ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ ያገኙትን ማበረታዎች (ተሽከርካሪ፣ የግንባታ እና ካፒታል ዕቃ) ተመሳሳይ የጉሙሩክ ቀረጥ ነፃ መብት ላለዉ ባለሀብት(ድርጅት) ለማስተላለፍ  ጥያቄ ሲቀርብ በደንብና  መመርያ መሠረት አስፈላግዉ  ቅድመ ሁኔታ ተሟልቶ ስለመቅረቡ ተጣርቶ  የዝዉዉር ድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
  • ያለዉጪ ምንዛሪ ክፍያ ማበረታቻ ወደ ሀገር ዉስጥ የማስገባት  መብት ላላቸዉ ባለሀብቶች በደንብና  መመርያ መሠረት አስፈላግዉን  ቅድመ ሁኔታ አሟልተዉ ሲቀርቡ  የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት
  • የገቢ ግብር እፎይታ  አገልግሎት ለሚጠይቁ ባለሀብቶች በደንብና  መመርያ መሠረት አስፈላግዉን  ቅድመ ሁኔታ አሟልተዉ ሲቀርቡ  የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት

ለ. አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች

  • የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሲዳማ ክልል የወጣ ከሆነ በማመልከቻ ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሀዋሳ ከተማ  የወጣ ከሆነ ባለሀብቶች ከሀዋሳ ከተማ ኢንቨስትመንት ማስፋፍ /ቤት የድጋፍ ዳብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ ለዚህ አገልግሎት በዳይረክቶሬቱ በተዘጋጀ ፎርም ሞልቶ ማቅረብ
  • ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚዉል  ተሽከርካሪ ካፒታል ዕቃ እና አክሰሰሪ ከዉጭ ሀገር መገዛቱን የሚገልጽ ሰነድ በኦን-ላይን ላይ በማስገባት ያመለክታል፤
  • የግዥ ደረሰኝ
  • ቢል ኦፍ ሎድንግ
  • ፓክንግ ሊስት
  • ትራክዋይ ቢል
  • ለመኪና ግዥ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ዲክላራሶን ማቅረብ ያስፈልጋል
  • ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚዉል  ተሽከርካሪ ካፒታል ዕቃ እና አክሰሰሪ ከዉጭ ሀገር ለማስገባት ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች በኢትዮጵያ የአንድ መስኮት አገልግሎት ሲዳማ ክልል መንግስት ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኦን-ላይን ሲስተም ላይ በማስገባት ማመልከት

ሐ. ካፒታል ዕቃ ከሀገር ዉስጥ የተገዛ ከሆነ-

  • የግዥ ዉል ሰነድ ማቅረብ
  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ
  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ  ምስክር ወረቀት ማቅረብ
  • በዘመኑ የታደሰ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ  ምስክር ወረቀት ማቅረብ
  • የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት
  • ለግዥ የተከፈለ ደረሰኝ ማቅረብ

 

  1. ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነፃ ያገኙትን ማበረታዎች (ተሽከርካሪ፣ የግንባታ እና ካፒታል ዕቃ) ተመሳሳይ የጉሙሩክ ቀረጥ ነፃ መብት ላለዉ ሰዉ(ድርት) ለማስተላለፍ  ጥያቄ ሲቀርብ በደንብና  መመ መሠረት አስፈላግዉን  አገልግሎት ለማግኘት-
  • የሁለቱም ወገን የኢንቨስትመንት ፈቃድ በዘመኑ የታደሰ ማቅረብ
  • የግዥ ዉል ሰነድ ማቅረብ
  • ከሲዳማ ክልል ዉጭ መኪናም ይሁን ለሎች እቃዎችን ለማዛወር ከሆነ ሻጪ ባለሀብት የኢንቨስትመንት ቃድ ካወጣበት ኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ኮሚሽን ወይም /ቤት የስምምነት ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል
  •  ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ዝዉዉርን ከመፍቀድ በፊት ማበረታቻ የተጠየቀበት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ያለበት የልማት ደረጃ ታይቶ የሚወሰን ይሆናል፡፡

መ. ያለዉጪ ምንዛሪ ክፍያ ማበረታቻ ወደ ሀገር ዉስጥ የማስገባት  መብት ያላቸዉ ባለሀብቶች  አገልግሎቱን ለማግኘት-

  • እንደዕቃዉ አይነት አግባብ ባለዉ ተቆጣጣሪ /ቤት የሚሰጠዉ ማስረጃ ማቅረብ
  • ያለዉጪ ምንዛሪ ክፍያ እንዲገባ የሚጠየቀዉ ዕቃ ወደ ሀገር ከመግባቱ አስቀድሞ ስለመፈቀዱ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ
  •  በሀገ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመግቢያ ወደብ ወደ ሀገር የመጡ ወይም በቀጥታ በሀገ የተቋቋሙ ደረቅ  ወደቦች የተከማቹ ዕቃዎች በወደቡ መጋዘን እያሉ ለዕቃዎቹ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች አሟልቶ ማቅረብ፡፡

ሠ. የገቢ ግብር እፎይታ አገልግሎት ለማግኘት ባለሀብቱ

  • ለኮሚሽኑ ማመልከቻ በማቅረብ ፎርም መሙላት
  • ከተሰማራበት አካባቢ ኢንቨስትመንት /ቤት የምርቱን አይነት እንድሁም ማምረት የጀመረበት ቀን ወር እና . ተጠቅሶ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ
  • የንግድ ሥራ ፍቃድ በዘመኑ የታደሰ ማቅረብ
  • የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም ህጋዊ የኪራይ ዉል ማቅረብ
  • የተጨማር እሴት ታክስ ሰርተፍከት  ማቅረብ
  • የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር 
  • አገር ዉስጥ የሸጣቸዉ የመጀመሪያዎቹ 3/ሶስት/ ደረሰኞች እና Z-Report